News News
Minimize Maximize
« Back

አረንጓዴዋ ከተማ

በእርስዎ እይታ በአለማችን ከሚገኙ ከተሞች መካከል ሁለንተናዊ የከተማ እድገት ማስመዝገብ ችላለች ብለው የሚያምኑባት ከተማ ማን ትሆን፡፡ የምእራባዊያን ከተሞች ለንደን፣ ፓሪስ፣ ፍራንክፈረት፣ ወይንስ ኒው ዮርክ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ዱባይ፣ ዶሃ፣ ሪያድ፤ ወይንስ የሩቅ ምስራቆቹ ሆንኮንግ፣ ኳላላንፑር፣ ቶኪዮና ሲዎል፡፡ ምናልባት ምደግሞ ምርጫዎ ከአፍሪካ ከተሞች መካከል ደርባን፣ ጆሃንስበርግ፣ ሞምባሳ ወይም ካይሮ ይሆኑ በአለማችን ውጤታማ የከተማ ልማት ስትራተጂን በመንደፍ አካባቢ ጥበቃን እንዲሁም የከተሞች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን ባጣጣመ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የሆኑ በርካታ ከተሞች አሉ፡፡ ከነዚህ ከተሞች መካከል ስኬታማ የከተማ ልማት ስትራተጂ በመንደፍ ለግማሽ ምእተ አመት የዘለቀ ተጨባጭና ፈጣን የከተማ እድገት ማስመዝገብ የቻለችና ላደጉ ሀገራት ሳይቀር በተምሳሌትነት ስሟ በስፋ የሚነሳና ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣት ለአለም ከተሞች ተምሳሌት የሆነች ከተማ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል፡፡

የከተማዋ ታሪክ

ከተማዋ በብራዚል ፓራና ተብሎ በሚጠራው ግዛት ከሚገኙ ከተሞች መካከል በግዝፈቷ ትጠቀሳለች፡፡ እ/ኤ/አ በ2015 የተጠናው የህዝብ ቁጥር መረጃ እንደሚያሳየውም በከተማዋ የሚገኘው የህዝብ ቁጥር ወደ ሶስት ሚሊዮን ተጠግቷል፡፡ ከተማዋ ስያሜዋን ያገኘችው በብዛት በምታበቅለው የቴምር ዛፍ አማካኝነት ነው፡፡ የቴምር ምድር ማለት ነው፡፡ ከተማዋ ባጠቃላይ 432 ስኩኤር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋ አላት፡፡ የከተማዋ እብዛኛው ክፍል ሜዳ ሲሆን ዙሪያውን በተራራ የተከበበ ሲሆን በአማካኝ ከተማዋ ከባህር ጠለል በላይ 934 ከፍታ ላይ ነው የምትገኘው፡፡ የከተማዋን የአየር ንብረት ስንመለከት ከተማዋ በከፍታ ቦታ ላይ የተቀለሰች ከተማ እንደመሆንዋ በቀዝቃዛ ወራት ከ7 -0 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ ቅዝቃዜ ታስተናግዳለች፡፡ ይሁን እንጂ በበጋ ወራት ያለው ሙቀት ከ 25 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ እይበልጥም ይህም ለኑሮ እጅግ ተስማሚ አድርጓታል፡፡ ከተማዋ መጠሪያዋን ያገኘችው ፖርቱጋሎች እ/ኤ/አ ከ1693 ዓ.ም በአካባቢው ላይ ከሰፈሩ በኋላ ቢሆንም በይፋ ከተማ ተብላ የተዋቀረችው ግን እ/ኤ/አ ከ1882 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡

የህዝብ ቁጥር

መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ/አ/አ በ1950 በከተማዋ ይኖር የነበረው የህዝብ ቁትር ከ180 ሺህ የበለጠ አልነበረም፡፡ የሁን እንጂ የዚህች ከተማ የህዝብ ቁጥር በየ 10 አመቱ በእጥፍ እያደገ የመጣ ሲሆን እ/አ/አ በ2015 ከ2 ሚሊዮን በላይ ሆኗል፡፡ የህንንም ስናይ የከተማው ነዋሪ በ60 አመት ውስጥ በ1 ሺህ እጥፍ አድጓል ማለት ነው፡፡ ይህ የከተሜነት እድገትም እስካሁን አለም ከተመዘገቡት ቀዳሚ ነው፡፡

ኢኮኖሚ

የከተማው አስተዳደር ውጤታማ ተብሎ የሚነገርለትን የከተማውን ማስተር ፕላን ነድፈው ወደስራ የገቡት እ/ኤ/አ በ1968 ነበር፡፡ በዚህም በከተማ ስራ እድል ፈጠራ፣ መሰረተ ልማት፣ በቤት አቅርቦትና በአካባቢ ጥበቃ አስገራሚ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ የከተማዋ የኢኮኖሚ እድገት ስንመለከት ምንም እንኳ ብራዚል እንደሃገር ለአስርት ዓመት ከ4 በመቶ ያልበለጠ እድገት እያስመዘገበች ብትመጣም ይህች ተአምረኛ ከተማ ግን በተከታታይ ለ30 ተከታታይ አመታት ከ7 በመቶ በላይ እድገት እያስመዘገበች መጥታለች፡፡ የከተማዋ ኢኮኖሚ እ/ኤ/አ ከ1975 እስከ 1995 ብቻ በ75 በመቶ ማደግ ችሏል፡፡ ለዚህም ነው በዚህች ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች የነብስ ወከፍ ገቢ ከተቀረው የብራዚል ነዋሪዎች በአማካኝ ከ66 በመቶ በላይ ብልጫ ሊያስመዘግብ የቻለው፡፡ ከተማዋ ባስመዘገበችው እድገት በሚያስደንቅ መልኩ የከተማዋን ነዋሪዎች የመጀመሪያ የእድገቱ ተጠቃሚ ማድረግ ችላለች፡፡ ለዚህም እንደማሳያ የከተማው ነዋሪዎች ነፃ የጤና ሽፋን፣ የትምህርት፣ ቤተመፃህፍትና ተዛማጅ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል፡፡ በከተማዋ በስፋት የተገነቡት ህንፃዎችም ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ፣ መዝናኛና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችሉ ተደርጎ ነው፡፡ በከተማዋ ያሉ ዩንቨርሲቲዎችም በተለይ በአካባቢ ጥበቃ፣ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግና ሙያ ነክ በሆኑ ትምህርቶች ላይ በቅናሽ ዋጋ የትምህርት እድል ይሰጣሉ፡፡ በጣም የሚያስደንቀው ደግሞ ከተማዋ የነዋሪዎቿን ገቢ ለማሳደግ የተከተለችው የኢኮኖሚ ስትራተጂ ነው፡፡ ከተማዋ የነዋሪዎቿን ገቢ ለማሳደግና ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር ፖሊሲ በመቅረፅና ዋና የከተማዋ ስትርተጂክ ፕላን በማድረግ መንቀሳቀስ የጀመረችው እ/ኤ/አ በ1990ዎቹ ነው፡፡ኩሪቲባ እንደ ከተማ ከተዋቀረችበት ግዜ ጀምሮም ቀጣይነት ያለው የከተማ ልማት ስትራተጂ ተግባራዊ በማድረግና በተለያዩ ግዜያትም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ ተከታታይ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገበች የመጣች ከተማ ናት፡፡ በተለይም ደግሞ በከተማ የትራፊክ እንቅስቃሴና በአካባቢ ጥበቃ ያስመዘገበችው ስኬት ለብዙ ሀገራት ሞዴል ለመሆን ችሏል፡፡ በተጨማሪም ከአካባቢ ጥበቃ ስራ ጋር በማይጣላ መልኩ የተቀለሱ በርካታ ኢንደስትሪዎች በከተማዋ ይገኛሉ፡፡ የከተማዋ ኢኮኖሚም የተቀለሰው ኢንደስትሪ፣ ንግድና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ ከተማዋ በቱሪዝም የምታገኘው ገቢም ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ባሳለፍናቸው 10 አመታት ብቻ በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ ጎብኚዎች ስታስተናግድ ነው የቆየችው፡፡ ከተማዋ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የከተማ እድገት ከሚያመጣቸው ቀውሶች ለማዳን ሲባል በተለይ ከትራንስፖርት መጨናነቅ፣ ከህዝብ ቁጥር መናር፣ ከዋጋ ግሽበት፣ ከአየር ብክለት፣ ከፅዳት መጓደልና ከመሳሰሉ የከተማ ኢኮኖሚ እድገት ተከትለው ከሚመጡ ችግሮች ለመታደግ ሲባልም በተለያዩ ግዜያት የተለያዩ የከተማ ፕላን ማሻሻያዎችን ተግባዊ እድርጋለች በዚህም ጉልህ የሚባል ውጤቶች እግኝተዋል፡፡

የቤቶች ፕሮግራም

በከተማዋ ከተሰሩ ውጤታማ የከተማ ልማት ሰራዎች መካከል የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ነው፡፡ በተለይ የከተማው የህዝብ ቁጥር በፍጥነት እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለነዋሪው ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት ማቅረብ አነዱ ስራ ነበር፡፡ ለዚህም የከተማው አስተዳደር ሁለት ስትራተጂዎችን ነድፎ ወደስራ ገብቷል፡፡ 1ኛው መካከለኛና ከዛ በላይ ገቢ ያላቸው ዜጎች መንግስት የተወሰኑ ድጎማዎችን በማድረግ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችለው አሰራር ሲሆን 2ኛው ደግሞ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች መሰረት ያደረገ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ደረጃ በመንግስት ይደጎማል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ይህን አገልግሎት ለማግኘት ከተመዘገቡት ዜጎብ መካከል 70 በመቶ ያህሉ ቤት ማግኘት ችለዋል፡፡ በአጠቃላይ በከተማው የሚገኘውን እ/አ/አ በ1970 ከነበረው የመኖሪያ ቤት የ1ሺ በመቶ ያክል ብልጫ አለው፡፡ ይህም ባደጉ ሀገራት ሳይቀር ግርምት ፈጥሯል፡፡ሌላው እ/አ/አ ከ1990 ጀምሮ በከተማዋ አስተዳደር በከፍተኛ ደረጃ የሚደጎም የቤቶች ፕሮጋግራም በድጋሚ የተጀመረ ሲሆን በዚህም በከተማዋ ያለውን የቤት ጥያቄ በአንፃራዊነት መፍታት ችለዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በግል ለሚገነቡ የከተማው ነዋሪዎች መንግስት ያወጣቸውን ፕላኖች መሰረት እድርገው የሚገነቡ ሲሆን ለዚህም ለእያንዳንዱ ቤተ ሰሪ የግንባታ አማካሪ ስለሚመደብ የተገነቡት መኖሪያ ቤቶች ጥራት፣ ቦታ አጠቃቀምና ውበትን የተላበሱ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡

የገጠር ቤቶች ልማት ፕሮግራም

የገጠር ቤቶች ልማት ፕሮግራም የተጀመረው እ/አ/አ በ1994 ሲሆን አላማውም በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ የገጠር መንደሮችን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰርና በመጠነኛ ዋጋ ቤቶችን በመገንባት በከተማ ውስጥ ቤት ለመግዛትም ሆነ ለመከራየት አቅም ለሌላቸው ዜጎች በመጠነኛ ዋጋ በነዚህ የገጠር መንደሮች ቤት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡

መሰረተ ልማት

በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ የጤና፣ የመብራት፣ ኢንተርኔትና የትምህርት ሽፋን ይሰጣል፡፡ በከተማዋ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ስንምለከት በአጠቃላይ አለም አቀፍ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ 10 ከፍተኛ ዩንቨርሲቲዎች ሲገኙ በተጨማሪም በርካታ የግል ኮሌጆች አሉ፡፡ ኩሪቲባ በአለማችን ምቹ የትራንስፖርት ዝርጋታን ተግባራዊ ካደረጉ ከተሞች በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡ በተለይም በከተማዋ በእያንዳንዱ አቅጣጫ የተሸከርካሪዎችን አይነት፣ ማቆሚያ ቦታና የእግረኛ መንገዶችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተገነቡት ሰፋፊ መንገዶች ይጠቀሳሉ፡፡ የትራፊክ ፍሰቱን ለመቀነስና ምቹ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠትም በከተማዋ ለመደበኛ ተሽከርካሪዎች ከተገነቡት መንገዶች ጎን ለጎን በሶስት አቅጣጫዎች የተከፈለ ለህዝብ በቅናሽ ዋጋ አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ መገልገያ አውቶቡሶች ብቻ የሚጓዙባቸው መንገዶች ይገኛሉ፡፡ በነዚህ መንገዶች ውስጥ ሌሎች መኪኖች መግባት ስለማይችሉ የከተማው ነዋሪዎች ባሰቡት ሰአት ከፈለጉበት ስፍራ መድረስ ያስችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም አገልግሎት አሰጣጣቸው የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ መሆኑና ወደሁሉም የከተማው አቅጣጫ ለመጓዝ ቅናሽና ወጥ የአከፋፋል ስርአት መከተላቸው አገልግሎቱን የበለጠ ቀልጣፋና ምቹ አድርጎታል፡፡

ከተማዋ ለከተማ አውቶብሶች ብቻ የተገነባ መንገድ(BRT) ለአለም አስተዋውቃለች፡፡ ይህም ያመጣውን ውጤት ስንመከት በርካታ መኪና ያላቸው የከተማው ነዋሪዎች አዘውትረው እነዚህን አውቶብሶች እንዲጠቀሙ እድል ስለከፈተ በከተማዋ በአመት 27 ሚሊዮን አላስፈላጊ የመኪኖች ጉዞ ለማስቀረት ችሏል፡፡ እንግዲህ ይታያችሁ የአንድ አውቶሞቢል ጉዞ በእንድ ሊትር ነዳጅ ብናሰላው እንኳ በአመት 27 ሚሊዮን ነዳጅ ለማዳን ያስችላል ማለት ነው፡፡ የከተማዋን የካርቦን ልቀት በመቀነስ ረገድ ደግሞ ያመጣው ለውጥ በእርግጥም ከተማዋን ልዩ ይስብላታል፡፡ ለዚህም ይመስላል በርካታ የአለማችን ሀገሮች በፍጥነት ይህን ተሞክሮ በሀገራቸው ተግባራዊ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን የጀመሩት፡፡ በከተማዋ የሚገኙት 1ሺህ 1 መቶ የህዝብ አውቶብሶች በቀን በአማካኝ 12 ሺህ 5 መቶ ጉዞዎችን ያደርጋሉ ይህንም ቁጥር በተሳፋሪ ብዛት በቀላሉ ስናሰላው በቀን በአማካኝ 1.3 ሚሊዮን ነዋሪዎችን ከቦታ ቦታ ያደርሳል ማለት ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል 80 በመቶ የሚሆነው የከተማዋ ነዋሪ እነዚህን አውቶቡሶች የሚጠቀመው፡፡ ይህም በዋናነት ሁለት ጠቀሜታዎች አሉት ይህም በከተማው ያለውን የትራፊክ ፍሰት መቀነሱና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ያለውን የነዳጅ ፍጆታ መቀነስ መቻሉ ነው፡፡ ከተማዋ የሚያስፈልጋትን የነዳጅ አቅርቦት ከ4 በመቶ በላይ መቀነስ ችላለች፡፡ይህም በነዳጅ ምክንያት በከተማቸው ሊከሰት የሚችለውን የአየር ብክለት በ4 በመቶ መቀነስ ችለዋል ማለት ነው፡፡

አረንጓዴ ልማት

በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫ ለአረንጓዴ ልማት ሲባል የተተዉ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ ይህንም በቀላሉ ለመመልከት በእያንዳንዱ የከተማው ስፍራዎች በአመካኝ 54 ስኩዌር ሜትር አረንጓዴ ስፍራ ይገኛል ማለት ነው፡፡ በዚህም ከተማዋ ባጠቃላይ 400 ስኩኤር ኪሎሜትር ቦታን የሚሸፍን አረንጓዴ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮችና ጥብቅ ደኖች ባለቤት እንድትሆን አስችሏታል፡፡ በከተማዋ በስርአት የተተከሉ በርካታ ሀገር በቀልና የውጭ ሀገር ዛፎች ይገኛሉ፡፡ ባጠቀላይ 16 አረንጓዴ ፓርኮች፣ 14 ጥብቅ ደኖችና ከ1 ሺህ በላይ አረንጓዴ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ በከተማዋ ባሳለፍናቸው ሁለት አስርት አመታት ብቻ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ዛፎች ተተክለዋል፡፡ ይህም የከተማዋን የአየር ንብረት በእጅጉ ለማረጋጋት የቻለ ሲሆን በተጨማሪም ለከተማዋ ልዩ ውበት አላብሷታል፡፡

 

በከተማዋ የሚገኘው የአረንጓዴ ስፍራ በከተማው ከሚኖረው ነዋሪ ጋር ሲነፃፀርም እያንዳንዱ ዜጋ በነብስ ወከፍ 600 ስኩኤር ጫማ አረንጓዴ ስፍራ ይደርሰዋል፡፡ ይህም ከተማዋ በአለማችን ከሚገኙ ከተሞች በአረንጓዴነቷ ከአይስላንዷ ሬጃቪክና ከአሜሪካዋ ፖርትላንድ ቀጥላ የሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ እስችሏታል፡፡

የከተማዋ ፅዳት

ከተማዋ ከተጎናፀፈቻቸው በርካታ ስኬቶች መካከል በከተማ ፅዳት ዙሪያ ያከናወነቻቻው ተግባራት ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል በከተው በስፋት ተግባራዊ ተደርጎ ውጤት የተገኘበት (The "green exchange" employment program) ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ስራ እድል ፈጠራ እና አረንጓዴ ልማት ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህም ከከተማው የሚሰበሰበው ቆሻሻ በፍጥነት ከከተማው በማውጣትና ቆሻሻውን በፋብሪካዎች በየፈርጁ በመለየት መልሶ መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ቆሻሻቸውን በመግዛት የገቢ ምንጭ እዲፈጥሩ ማድረጋቸው ነው፡፡ ይህም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ከማገዙም ባሻገር የከተማውን ፅዳት በሚያስደስት መልኩ ለመጠበቅ ከማስቻሉም በሻገር ከአየር ብክለትና ከበሽታዎች የፀዳች ከተማ ለመገንባት አግዟቸዋል፡፡ በከተማዋ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው በየፈርጁ የልየታ ስራ ይሰራል ከዚህም ውስጥ ከ13 በመቶ በላይ የሚሆነው ቆሻሻ ማቀነባበሪያ ገብቶ ወደሌላ ግብአት ከተቀየረ በኋላ ለድጋሚ አገልግሎት ለገበያይቀርባሉ፡፡ ከተማዋ ባስመዘገበቻቸውም የከተማ ልማት ስኬቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ሞዴል በመሆን የበርካታ አለምአቀፍ ሽልማቶችን ለማግኘት ችላለች፡፡ እ/አ/አ በ2010 የአለም አቀፉ ስኬታማ የከተሞች ሽልማትን ለመግኘት ችላለች፡፡በቅርቡም ከተማዋ ተግባራዊ እድርጋ ውጤት ባስመዘገበችበት የመልሶ ማልማት ስራዎች በዩኒስኮ የአለም ከተሞች ተምሳሌት በመሆን ያገኘችው ሽልማት ይጠቀሳል፡፡